ስለድርጅቱ

የአደራ የህክምና ማዕከል በጥር 2000 ዓ.ም  በዶ/ር አባተ ባኔ የተመሰረ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሲሆን ደንበኛ ተኮር፣ በህክምናው ዘርፍ አመኔታ ያላቸው በተለይም በጨጓራ፤አንጀትና የጉበት ህመሞች ዙሪያ ስፔሻላይዝድ ባደረጉ የጤና ባለሙያዎች የተዋቀረ ነው፡፡ ድርጅቱን ሲያቋቁሙት በህክምናው ዘርፍ ሀገርን ለመጥቀም፣ ብዙ ባለሙያዎችን ለማፍራት፣ ጠቅላላ ህክምና ፣ የምርምር፣ የስልጠና ማዕከል መፍጠርን በማሰብ ነው።

አደራ እስካሁን ድረስ ለደንበኞቹ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ መስጠት አላማው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ለበርካታ የሀገሪቱ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

አሁን ሀገሪቷ ያለችበትን እድገትና በጤናው ዘርፍ የተሰጠውን ትኩረት ተከትሎ ያለውን አበረታች ሁኔታ በመጠቀም እንዲሁም ድርጅቱ ማህበሩን ለማገልገል ቁርጠኛ በመሆኑ ድርጅቱ ከእለት እለት እያደገ መጥቷል፡፡

ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች

የድርጅቱ ራዕይ

በ 2025 በምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም የህክምና የልቀት ማዕከል ሆኖ መገኘት

የድርጅቱ ተልዕኮ

አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የህክምና፣ የጤናና የስልጠና የምርምር ማዕከል በመገንባት የላቀ አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ለደንበኞችና ለባለድርሻ አካላት የላቀ እርካታን፤ ለባለቤቶች ዘላቂ እሴትን መጨመር እና የዜጎችን ጤና በመጠበቅ ለሀገር ልማት አስተዋዕኦ ማበርከት ነው፡፡

የድርጅቱ እሴቶች

  • ህሙማን ተኮር(patient focused)፣ በማንኛውም ጊዜ ደንበኞችን ለማስደሰት መስራት
  • ታማኝነት(integrity) ፣ ለድርጅቱ፣ ለደምበኛ እና ለባለድርሻ አካላት በታማኝነት ማገልገል
  • የቡድን መንፈስ(team work)፣ ለጋራ አላማ በጋራ በመስራት ውጤታማ መሆን
  • ተጠያቂነት(accountability)፤ በግለሰብም ሆነ በቡድን በተጠያቂነት መንፈስ ማገልገል
  • ልህቀት (Excellence)፤ ምንጊዜም አፈጻጸምን በላቀ ሁኔታ በመፈጸም የደንበኛን ዕርካታ ማረጋገጥ
  • ርህራሄ (compassionate)፣ የታካሚ ችግር የእኛም ጉዳይ ነወ በማለት በቅንነት ከልብ ማገልገል
  • የህክምና ስነምግባር ለህሙማን ክብር/respect፤ ለህሙማንን ክብርና ሚስጥር ጠባቂነት